Get Mystery Box with random crypto!

YeneTube

የሰርጥ አድራሻ: @yenetube
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 131.08K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-04-23 18:08:18
ህ.ወ.ሓ.ት ከብልጽግና ፓርቲ ጋር ለመቀላቀል ውይይት አላደረግኩም፤ መሰረታዊ ልዩነቶችም አሉን ሲል ገለጸ

የህወሓት እና የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች እያደረጉ የሚገኙት ውይይት "ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ የተፈጠረውን አንፃራዊ ሰላም ለማስፋት እና ለማጠናከር ያለመ ነው" ሲል ድርጅቱ ትላንት እና ዛሬ እየወጡ የሚገኙ ዘገባዎችን ዛሬ ባሰራጨው መግለጫ ማስተባበሉን አዲስ ማለዳ ተመልክታለች።

ህወሓት እና ብልጽግና ፓርቲ ለመዋሀድ ተከታታይ ውይይትና ድርድር እያደረጉ ይገኛሉ የሚሉ ዘገባዎች መውጣታቸው ይታወሳል።

አዲስ ማለዳ ከህወሓት አጭር መረጃ እንደተመለከተችው "ህወሓት እና ብልጽግና መሰረታዊ የዓላማ እና የአስተሳሰብ ልዩነት ያላቸው ፓርቲዎች ናቸው" በማለት በይፋዊ ገጹ ሰፍሯል።

ይኹን እንጁ ልዩነቶቹ እንዳሉ ሆኖ ሁለቱ ፓርቲዎች ሊወያዩባቸው የሚገቡ ብዙ አጀንዳዎች በመኖራቸው ተከታታይ ውይይት ተጀምሯል ተብሏል።

"ከዚህ ባለፈ ግን ህወሓት ከብልጽግና ጋር ለመቀላቀል ንግግሮች ተጀምረዋል የሚለው መረጃ ሙሉ በሙሉ ከእውነት የራቀ ነው" ሲል ድርጅቱ ማስታወቁን አዲስ ማለዳ ተመልክታለች።

ሕወሓት ገዥውን ፓርቲ ብልፅግና ለመቀላቀል ተከታታይ ድርድሮች እያደረገ ነው በሚሉት ዘገባዎች የሕወሓት ሊቀ መንበር ደብረፅዮን ገብረሚካዔል በአዲስ አበባ ተገኝተው ይህን ድርድር መጀመራቸው እና ከሁለት ሳምንታት በኋላ የብልፅግና ምክትል ሊቀ መንበር አደም ፋራህ ወደ መቀሌ ተጉዘው ድርድሩን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

እነዚሁ ዘገባዎች በህወሓት ውስጥ ብልፅግናን መቀላቀል “ስህተት ነው" በሚሉ እና "ውህደቱ ለትግራይ ችግሮች መፍትሄ ለማምጣት ጠቀሜታ አለው" በሚሉት ሃሳቦች መከፋፈል መኖሩን የጠቆሙ ቢሆንም ህወሓት ጉዳዩን ሙሉ በሙሉ አስተባብሏል።

@Yenetube @Fikerassefa
13.3K viewsedited  15:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-23 09:41:24 በኮሬ ዞን በቀጠለው ጥቃት አራት አርሶ አደሮች በታጣቂዎች መገደላቸው ተገለፀ!

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ፣ አራት ወጣት አርሶ አደሮች፣ ከምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ በተነሱ ታጣቂዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ።በእርሻ ሥራ ላይ እንደነበሩ የተገለጹት አርሶ አደሮች የተገደሉት፣ “ኦነግ ሸኔ” ባሏቸው ታጣቂዎች እንደኾነ፣ የኮሬ ዞን የሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ተፈራ ቦንዶራ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ ቆቦ ቀበሌ ትላንት ሚያዚያ 13 ተገደሉ ከተባሉ አራት ወጣት አርሶ አደሮች ውስጥ ሁለቱ የወንድማቸው ልጆች እንደኾኑ አቶ ምትኩ ሽብሩ በስልክ ለአሜሪካ ድምፅ በስልክ ገልፀዋል።

አራቱም የሁለት ቤተሰብ አባላት መኾናቸውን፣ የሟቾቹን ስም በመዘርዘር የገለፁት አቶ ምትኩ እርስ በርሳቸውም ዘመዳማቾች መኾናቸውን አክለዋል። ለጥቃቱ ጉጂ ዞን ውስጥ ይንቀሳቀሳሉ ያሏቸውን ታጣቂዎችን ተጠያቂ ያደረጉት አቶ ምትኩ፣ ይህን የሚያስቆም ኃይል ባለመኖሩ ሕዝቡ ስጋት ላይ መውደቁን ገልፀዋል።

አቶ አጋፋሪ መንገሻ የተባሉ የቆቦ ቀበሌ ነዋሪ የእርሻ ማሳቸውን አረም በሚያርሙበት እና ከብቶቻቸውን በሚጠብቁበት ወቅት እንደተገደሉ ተናግረዋል።

አቶ አጋፋሪ ተዘርፈዋል የተባሉ ከብቶች እና ሌሎች ንብረቶች ወደ ገላን ወረዳ እንደተወሰዱባቸው ገልፀው ክስ አሰምተዋል። ባለፈው ሳምንት የ13 ዓመት አዳጊ እና ሌላ አርሶ ከቆቦ ቀበሌ መገደላቸውን አቶ አጋፋሪ አስታውሰዋል።

የኮሬ ዞን ሰላም እና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ተፈራ ቦንዶራ በግብርና ሥራቸው ላይ የነበሩ አራት አርሶ አደሮች የተገደሉት ሸኔ ሲሉ በጠሯቸው የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ታጣቂዎች መኾኑን ተናግረዋል።አቶ ተፈራ አክለው ካለፈው ሚያዚያ 8/2016 ዓ.ም ጀምሮ፣ በአንድ ሳምንት ውስጥ ሰባት አርሶ አደሮች ዳኖ ፣ መቅሬዲ እና ቆቦ ከተሰኙ ቀበሌዎች ያልታጠቁ ሲቪሎች በታጣቂዎች መገደላቸውን አክለው ገልጸዋል::

ስለ ጉዳዩ ከአፋን ኦሮሞ ክፍል ባልደረባ ነሞ ዳንዲ የተጠየቁት፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትም፣ በዓለም አቀፍ ቃል አቀባዩ አቶ ኦዳ ተርቢ ክሱን አስተባብለዋል። ከምዕራብ ጉጂ ዞን ባለሥልጣናት አስተያየትና ምላሽ ለማካተት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም::ይሁን እንጂ ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ጉዳይ የተጠየቁት የአካባቢው ባለሥልጣናት፣ ቀበሌዎቹ በሸማቂዎች በሚደርሰው ጥቃት የተነሳ ከቁጥጥር ውጭ መኾኑና ለኅብረተሰቡ መግሥታዊ አገልግሎት መስጠት እንዳልተቻለ መናገራቸው ይታወሳል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
13.1K views06:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-23 08:35:55
መልዕክት ወደ ክልል ከተሞች ይላኩ ይቀበሉ።
#ፈጥን #ቀላል እና #አስተማማኝ
ቁ.1 አዲስ አበባ ከጎላጎል ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ኳሊቲ ህንፃ
0962627762 -ሀዋሳ
0980526262 - ወላይታ ሶዶ
0988627762 - አርባምንጭ
0925636333 - ቦረና
0980526262 - አዳማ
13.1K viewsedited  05:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-22 15:54:16
በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎንደር ዞን ውስጥ በሚገኘው የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ከሦስት ቀናት በፊት የተነሳው እሳት መቆጣጠር አለመቻሉ ተገልጿል።

ሚያዚያ 10፣ 2016 ዓ.ም. በስፍራው የተነሳው እሳት በቁጥጥር ሥር አለማዋሉን የክልሉ ባለሥልጣን ገለጹ።የክልሉ የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ የሆኑት አባይ መንግሥቴ ለቢቢሲ እንደተናገሩት እሳቱ ከተነሳበት ቀን ጀምሮ የአካባቢው ማኅበረሰብ እና አመራሮች ለማጥፋት ጥረት ቢያደርጉም እሳቱን መቆጣጠር አልተቻለም።

“የቦታው አቀማመጥ አስቸጋሪ በመሆኑ ጠፋ ሲባል እንደገና እየተነሳ በቁጥጥር ሥር ማዋል አልተቻለም” ብለዋል።ሆኖም እሳቱ ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይስፋፋ የአሰሳ እና የጥበቃ ሥራ እየተሠራ ነው ያሉት ኃላፊው፣ እሳቱ ከቁጥጥር ውጪ አለመውጣቱን ተናግረዋል።

በፓርኩ የእሳት አደጋ ሲከሰት ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ አይደለም።
ከአምስት ዓመታት በፊት በፓርኩ ከፍተኛ እሳት ተነስቶ ከክልሉ እና ከፌደራል አቅም በላይ ሆኖ የእስራኤል እና የኬንያ እሳት ማጥፊያ ሄሊኮፕተርን ድጋፍ እስከ መጠየቅ ተደርሶ ነበር።

@YeneTube @FikerAssefa
15.4K views12:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-22 13:45:26
በፒያሳ ለኮሪደር ልማት የፈረሱ ሰፈሮችን ጨምሮ በከተማው በርካታ ቦታዎች የሊዝ ጨረታ ወጣ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ፣ በአራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ ከአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም ፊት ለፊት ለኮሪደር ልማት በሚል የፈረሱ ሰፈሮችን ጨምሮ ከ250 በላይ በሚሆኑ ቦታዎች ላይ የሊዝ ጨረታ ማውጣቱን ዋዜማ ከተመለከተችው የጨረታው ሰነድ ተረድታለች።

የሊዝ ጨረታው ከለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ውጭ በተቀሩት የከተማው አስር ክፍለ ከተሞች ባሉ ቦታዎች ላይ ወጥቷል። የሊዝ ጨረታው ለአመታት ከተቋረጠ በኋላ ሲወጣ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።የጨረታው ሰነድም ከረቡዕ ሚያዝያ 9 2016 አ.ም ጀምሮ መሸጥ የተጀመረ ሲሆን ፣ የሰነድ ሽያጩ እስከ ሚያዝያ 24 ቀን 2016 አ.ም ድረስ እንደሚቀጥል ተነግሯል።

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
15.5K views10:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-22 13:17:38 የአማራ ክልል መንግሥት ለሕዝቡ ጥሪ አቀረበ።

የሕወሓት ታጣቂ ቡድን የሰላም አማራጮችን ወደ ጎን በመተው የማንነት ጥያቄ ያለባቸውን የራያ አላማጣ፣ የራያ ባላ፣ ኦፍላ፣ ኮረም እና ዛታ አካባቢዎችን በወረራ ይዟል::

ይህንን ተከትሎ የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ የአማራ ሕዝብ ዛሬም እንደትላንቱ ከሀሰት ፕሮፓጋንዳ እና ከሰርጎ ገቦች ራሱን እና አካባቢውን እንዲጠብቅ ጥሪ አስተላልፏል::

ሕዝቡ ከክልሉ መንግሥት እና በየአካባቢው ከሚገኙ አስተዳደሮች ጋር የጠበቀ ቁርኝት በመፍጠር ጠላቶቹ የከፈቱበትን ጥቃት ለመመከት በሚደረገው ጥረት የድርሻውን እንዲወጣ ነው ጥሪ ያደረገው::

የክልሉ መንግሥት ከአማራ ሕዝብ በተጨማሪ ለፌደራል መንግሥት እና ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ጥሪ አቅርቧል፤ ለፌደራል መንግሥት ባስተላለፈው ጥሪ የሕወሓት ታጣቂ ቡድን በወረራ ከያዛቸው ቦታዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ለቆ እንዲወጣ እና ሕዝቡን ከጥፋት መታደግ እና የሀገሪቱን ሉዓላዊነት መታደግ እንደሚገባ ጠቁሟል::

ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ደግሞ ሕወሓት በክልሉ ሕዝብ ላይ የፈጸመውን ወረራ በጥብቅ እንዲያወግዝ እና ከክልሉ ሕዝብ ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርቧል።

@Yenetube @Fikerassefa
14.5K viewsedited  10:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-22 13:14:28 የመስተንግዶ ባለሙያዎች የአለባበስ ኮድ መመሪያ ዝግጅት በመጠናቀቁ በቅርቡ ፀድቆ ተግባራዊ ይሆናል ተባለ፡፡

በሆቴሎች የሚሠሩ ሴት የመስተንግዶ ባለሙያዎች ከሀገሪቱ ባሕል ውጪ የሆነውን አለባበሳቸውን ለማስተካከል የሚያስችል የአለባበስ ኮድ መመሪያ ዝግጅቱ በመጠናቀቁ በቅርቡ ፀድቆ ተግባራዊ እንደሚደረግ የአዲስ አበባ ባሕል፣ ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ገለጸ።

የአዲስ አበባ ባሕል፣ ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሣው (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በአንዳንድ ሆቴሎች የሴት መስተንግዶ ሠራተኞች አለባበስ ከሀገሪቱ ባሕል ወጣ ያለ ነው።

ይህን ለማስተካከል የሚረዳ የመስተንግዶ ባለሙያዎች የአለባበስ ኮድ መመሪያ ዝግጅቱ ተጠናቆ ለከንቲባ ጽሕፈት ቤት እንዲፀድቅ በመላኩ መመሪያው በከተማዋ ካቢኔ በቅርቡ ፀድቆ ተግባራዊ እንደሚደረግ ይጠበቃል ብለዋል።

ለቱሪስቶች መስተንግዶ ሲሰጥ የሀገራችንን ባሕልና እሴት በጠበቀ መልኩ መሆን አለበት ያሉት ኃላፊዋ፤ በሆቴሎች ያለው የመስተንግዶ ባለሙያዎች አለባበስ ሥነ-ሥርዓቱን የጠበቀ መሆን እንዳለበት ተናግረዋል።

ሂሩት (ዶ/ር)እንዳመላከቱት፤ አሁን ላይ የመስተንግዶ ባለሙያዎች በተለይም ሴቶች በአንዳንድ ሆቴሎች አማካኝነት ሥነ-ሥርዓቱን ያልጠበቀ አለባበስ እንዲለብሱ ይገደዳሉ። ድርጊቱ ከሴት ልጅ መብት አኳያ ክብርን ያልጠበቀ እና አሳፋሪ ነው ብለዋል።

መመሪያው ፀድቆ ሥራ ላይ ሲውል በሆቴሎች የሚሠሩ የመስተንግዶ ባለሙያዎች ወጥ የሆነ ዓለማቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የአለባበስ ኮድ እንዲከተሉ ይደረጋል ያሉት ኃላፊዋ፤ ይህም የኢትዮጵያን ባሕልና ወግ ያልጠበቀ የአለባበስ ሥነ ሥርዓትን ለመቆጣጠር እንደሚያስችል አስረድተዋል።

አሁን ላይ በአንዳንድ ሆቴሎች የሚታየውን ከባሕል ያፈነገጠ የመስተንግዶ ባለሙያዎች አለባበስ መስተካከል እንዳለበት የከተማው ነዋሪዎች ጥያቄ እንደሚያቀርቡ ገልጸው፤ መመሪያው ሲፀድቅ የሁሉንም ጥያቄ እንደሚመልስ አብራርተዋል። ሕጉ ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣትም ጭምር ያለው በመሆኑ መመሪያውን በሚተላለፉ ላይ ቅጣት እንደሚጣል ጠቁመዋል።

የአለባበስ መመሪያውን ለማውጣት ቢሮው ሁለት ዓመት ሲሠራ መቆየቱን ተናግረው፤ ሕጉ ከፀደቀ በኋላ ወደ ርምጃ እንደሚገባ አመላክተዋል። ሕጉ እስኪፀድቅ የቁጥጥር ሥራ የሚሠራ ሲሆን በሚደረገው ክትትልና ድጋፍም አሁን ላይ ለውጦች መኖራቸውን ተናግረዋል።

በቱሪዝም ዘርፉ ውድድር በዓለም አቀፍ ይዘት ያለው በመሆኑ ደረጃውን ያልጠበቀ መስተንግዶ የሚሰጥ ከሆነ ቱሪስቶች ተመልሰው እንደማይመጡ የሚገልጹት ሂሩት (ዶ/ር)፤ በሆቴሎች መልካም መስተንግዶ እንዲሰጥ ለማስቻል ቢሮው በየዓመቱ ሁለት ሺህ ለሚደርሱ በሥራ ላይ ላሉ መስተንግዶ ሰጪ ባለሙያዎች ሥልጠና እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።

በከተማዋ ያሉ ዓለም አቀፍ ሆቴሎች የመስተንግዶ ባለሙያዎቻቸው አለባበስ ጥሩ መሆኑን ጠቅሰው፤ በመጠኑ ከሴት የመስተንግዶ ባለሙያዎች የፀጉር አያያዝ ሥነ-ሥርዓት ጋር በተያያዘ የማይፈቀዱ ነገሮች በአንዳንድ ሆቴሎች የሚታዩ በመሆኑ እንዲሻሻሉ ክትትል ይደረጋል ብለዋል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
14.1K views10:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-22 08:46:51
የአሜሪካው ም/ቤት የ95 ቢሊዮን ዶላር የውጪ ዕርዳታ አጸደቀ!

በአሜሪካ የተወካዮች ም/ቤት ለዩክሬን እና ለእስራኤል የሚሰጥን የ95 ቢሊዮን ዶላር የዕርዳታ ጥቅል ሕግ ከወራት ሙግት በኋላ ትናንት ቅዳሜ አጽድቋል።በኮንግረስ ያሉ መሪዎች ከቀኝ ዘመም ወግ አጥባቂዎች የደረሰባቸውን ተቃውሞ ወደ ጎን በማለት፣ ብዙም ባልተለመደ ሁኔታ ቅዳሜ ዕለት በተገናኘው ም/ቤት ሕጉን እንዲጸድቅ አድርገዋል።

አሁን የቀረው ሕጉን ወደ ሕግ አውጪው ሸንጎ ወይም ሴኔቱ መላክ ሲሆን፣ በዲሞክራቶቹ ቁጥጥር ስር ያለው ሴኔት እስከ ማክሰኞ ድረስ እንደሚያጸድቀው ይጠበቃል።

ከፓርቲያቸው ከፍተኛ ግፊት ያላባቸው ሪፐብሊካኑ የም/ቤቱ አፈጉባኤ ማይክ ጆንሰን፣ ወንበራቸውን እንደሚያጡ በፓርቲያቸው አባላት ዛቻ እየደረሰባቸው ሲሆን፣ ሕጉን ለማጽደቅ በተደረገው እያንዳንዱ እርምጃ የዲሞክራቶቹን ዕገዛ አግኝተዋል ተብሏል።

አራት ክፍሎች ያሉት ሕግ፣ ለዩክሬን፣ እስራኤል እና በኢንዶ ፓሲፊክ ለሚገኙ የአሜሪካ አጋሮች ገንዘብ የሚመድብ ሲሆን፣ ቲክ ቶክ በአሜሪካ ማኅበረሰብ ዘንድ ፈጥሯል የሚባለውንም ችግር የሚመለከት ነው።ሕጉ በም/ቤቱ የሚጸድቅ ከሆነ፣ በፊርማቸው እንደሚያጸኑት ፕሬዝደንት ባይደን ሲያስታውቁ ቆይተዋል።

[VoA]
@YeneTube @FikerAssefa
15.9K views05:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 21:13:42
"ታማሚው ስለማይድን የተሰበሰበውን ብር ሰይጣን አሳስቶን አጠፋነው. . ."

ይህንን ያለው 9,000 ሰው ተሰብስቦ በሚመለከተው የቲክቶክ ሽምግልና ላይ ነው።

ከሞተር ወድቆ ከወገብ በታች ለማይንቀሳቀሰው አለሙ ቢጫ የተባለ ታማሚ ግለሰብ የተለያዩ ታዋቂ ቲክቶከሮች የእርዳታ ገንዘብ ቢሰበስቡም ለታማሚው ብር ሳይደርስ ቀርቶ ታማሚው ባቀረበው ተማፅኖ ብሩን የሰበሰቡት ቲክቶከሮች የተወሰነ ብር ቢመልሱም ዋነኛው ወጣት ግን 350,000 ሺህ ብር አካባቢ ለመመለስ ፈቃደኛ አልሆነም። ለዚህም የቀረበው ምክንያት " ታማሚው ስለማይድን ብሩን አጥፍቼዋለሁ . . . ቲክቶክ አካውንቴን ሸጬ እከፍላለሁ" ብሏል።

Via: ስንታየሁ ኃይሉ
@Yenetube @Fikerassefa
15.3K views18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 19:56:52
የቡድን ሰባት ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ በርካታ አካባቢዎች ይታያሉ ያሏቸው፤ “የማያቋርጡ እና ኃይለኛ ውጥረቶች” እንደሚያሳስቧቸው ገለጹ።

በኢንዱስትሪ የበለጸጉት ሰባት አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ይፈጸማሉ የሚባሉ “የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እና በደሎች ሪፖርቶች”፣ “ብርቱ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ” እና “የምግብ ዋስትና እጦት መስፋፋት” እንዳሰጋቸውም አስታውቀዋል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በኢትዮጵያ ጉዳይ ስጋታቸውን ያንጸባረቁት፤ በጣልያኗ ካፕሪ ደሴት ያካሄዱትን ስብሰባ ሲያጠናቅቁ ዛሬ አርብ ምሽት ባወጡት መግለጫ ነው። ሚኒስትሮቹ በዚሁ መግለጫቸው፤ በኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት እና በህወሓት መካከል በተፈረመው ግጭት የማቆም ስምምነት አተገባበር ረገድ የተወሰዱ እርምጃዎችን በበጎ እንደሚቀበሉ ገልጸዋል።

በሰብዓዊ መብቶች እና በሲቪል ሰዎች ጥበቃ፣ ውጥረቶችን ለመፍታት በሚደረግ ፖለቲካዊ ውይይት፣ በዕርቅ፣ በብሔራዊ ውይይት፣ የሽግግር ፍትህ እና በግጭት ወቅት ወንጀል የፈጸሙ ተጠያቂ ለማድረግ፤ ተጨማሪ እና ዘላቂ እርምጃዎች ተግባራዊ እንዲደረጉ አበረታተዋል። በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች በመካሄድ ላይ በሚገኙ ግጭቶች የሚሳተፉ ወገኖች፤ በንግግር ሰላም ለማውረድ ተመሳሳይ ቁርጠኝነት እንዲኖራቸውም ጥሪ አቅርበዋል።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር )
@YeneTube @FikerAssefa
14.6K views16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ