Get Mystery Box with random crypto!

ዛሬ በመቀሌ ተጨማሪ የአየር ድብደባ መካሄዱን መንግስት አስታወቀ! የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዛሬ ከ | YeneTube

ዛሬ በመቀሌ ተጨማሪ የአየር ድብደባ መካሄዱን መንግስት አስታወቀ!

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዛሬ ከቀትር በኋላ በመቀሌ ከተማ በሚገኘው የቀድሞው የሰሜን እዝ ዋና መቀመጫ ግቢ ላይ የአየር ድብደባ ማካሄዱን መንግስት ይፋ አደረገ።

የመንግስት ኮሚንኬሽን አገልግሎት ኃላፊ የሆኑት ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) የአየር ድብደባው ከቀትር በኋላ መካሄዱን ለሪፖርተር አረጋግጠዋል።

የአየር ድብደባው የተካሄደው ቀደም ሲል የአገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን እዝ ዋና መቀመጫ በነበረው እና በአሁኑ ወቅት የህወሓት ኃይል ለወታደራዊ አገልግሎት በሚጠቀምበት ግቢ ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa