Get Mystery Box with random crypto!

እስክንድር ነጋ በደረሰበት ድብደባ ምክንያት ችሎት አለመቅረቡ ተገለፀ! በእነ እስክንድር ነጋ ላ | YeneTube

እስክንድር ነጋ በደረሰበት ድብደባ ምክንያት ችሎት አለመቅረቡ ተገለፀ!

በእነ እስክንድር ነጋ ላይ ምስክሮችን ማሰማት የጀመረው የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፀረ ሽብር እና ሕገ-መንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ከትላንት የቀጠለ ቀጠሮ ለዛሬ ሰጥቶ የነበረ ሲሆን በጠዋቱ ውሎ አንደኛው ተከሳሽ ስንታየሁ ቸኮል ባቀረበው ሪፖርት መሰረት እስክንድር ነጋ በትናንትናው እለት ምሽት እስር ቤት ውስጥ በደረሰበት ድብደባ ምክንያት ችሎቱ ላይ ሊገኝ መገኘት አለመቻሉ ተጠቅሷል።

ሪፖርቱ እንደተሰማ የእነ እስክንድርን ችሎት ለመከታተል የመጡት ታዳሚዎች ተቃውሞ በማሰማት ችሎቱን አቋርጠው መውጣታቸውን እና ችሎቱ መቋረጡንም የባልደራስ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ በቃሉ አጥናፉ(ዶ/ር) ለአዲስ ዘይቤ አረጋግጠዋል።

አያይዘውም እስክንድር ላይ የደረሰውን ድብደባ መንስዔ እና ተጠያቂ አካላቱን ጉዳይ ለማጣራት ጠበቃዎቹ ወደ እስር ቤት መሄዳቸውን የገለፁልን ሲሆን ችሎቱን አቋርጠው የወጡት ታዳሚዎች በፖሊስ ተይዘው ወደ አምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዳቸውንም ነግረውናል።

[@AddisZeybe]
@YeneTube @FikerAssefa