Get Mystery Box with random crypto!

ግብፅ እና ሱዳን የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ማካሄድ ጀመሩ! የግብፅ እና የሱዳን ወታደራዊ ኃይሎች ከ | YeneTube

ግብፅ እና ሱዳን የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ማካሄድ ጀመሩ!

የግብፅ እና የሱዳን ወታደራዊ ኃይሎች ከትናንት በስትያ ማክሰኞ የግብፅ ድንበር ጠባቂዎችና የሱዳን እግረኞችን ያካተተ የጋራ ልምምዶች መጀመራቸውን የግብፅ ጦር አስታወቋል።የጋራ ወታደራዊ ልምምዱ በሜድትራኒያን ግዛት በማትሮህ ግዛት በመሐመድ ናጉይብ የጦር ሰፈር መካሄዱም ተገልጿል።

ወታደራዊ ልምምዱ እስከ ጥቅምት 29 ድረስ እንደሚቀጥል የግብፅ ወታደራዊ ቃል አቀባይ ገብር አብደል ሃፌዝ መናገራችውን ሲጂቲን በድረገጹ አስነበቧል።

የመጀመሪያ ደረጃ ንድፈ ሃሳባዊ ንግግሮችን ጨምሮ ተግባራዊ ልምምዶችን እንዲሁም የድንበር ደህንነትን ለመጠበቅ እና ሰርጎ ገብነትን ለመዋጋት የሚያገለግሉ የጦር መሳሪያዎች የሚያጠቃልል ነው።አሁን የሚካሂደው የጋራ ልምምድ የሁለቱን ሃገራት የጋራ ዕድገት የማጠናከር ዓላማ ያለው ሲሆን ግብጽ ከወዳጅ አገራት ጋር ወታደራዊ ትብብርን ለማሳደግ ያላት ዕቅድ አካል ነውም ተብሏል።

Asham
@YeneTube @FikerAssefa