Get Mystery Box with random crypto!

ከቡና ወጪ ንግድ ከእቅድ በላይ ተጨማሪ 120 ሚሊየን ዶላር ተገኘ! በበጀት አመቱ የመጀመሪያ ሩብ | YeneTube

ከቡና ወጪ ንግድ ከእቅድ በላይ ተጨማሪ 120 ሚሊየን ዶላር ተገኘ!

በበጀት አመቱ የመጀመሪያ ሩብ ከቡና ወጪ ንግድ 330 ሚሊየን ዶላር በገኘቱን የቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) ለካፒታል ጋዜጣ ተናገሩ፡፡የገቢ መጠኑ በተጠቀሰው ጊዜ ይገኛል ተብሎ ከተጠበቀው መጠን ከግማሽ በላይ ጭማሪ የታየበት ነው፡፡

በሩብ አመቱ ልናሳካ ካቀድነው ተጨማሪ 120 ሚሊየን ዶላር አግኝተናል በዚህ ከቀጠልን በበጀት አመቱ በቀላሉ የአንድ ቢሊየን ዶላር ገቢን እናሳካለን፤ ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ አክለዋል፡፡

የብራዚል የቡና ምርት በአየር ንብረት ምክንያት መጎዳት የአለም የቡና ዋጋ እንዲያሻቅብ እያደረገው መሆኑ ይጠቀሳል፡፡ይህም ለገቢ ማደግ አስተዋፅኦ እንደነበረው የተገለጸ ሲሆን ፤በተጨማሪም ኢትዮጵያ የምትልከውን ቡና በከፍተኛ መጠን እየጨመረች ከመሆኑ ጋር ተያዞ የገቢ መጠኑን እያሳደገው ነው፡፡

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa