"YeneTube" Canal Télégramme

Logo de la chaîne télégraphique yenetube - YeneTube
665
Sujets de la chaîne :
Artland
Shegerhive
Ethiopia
Addisababa
Hiking
Logo de la chaîne télégraphique yenetube - YeneTube
Sujets de la chaîne :
Artland
Shegerhive
Ethiopia
Addisababa
Hiking

"YeneTube" Canal Télégramme

Adresse du canal : @yenetube
Catégories: Non classé
Abonnés: 168,681 (Date de mise à jour: 2021-10-22)
Description de la chaîne

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Commentaires

Vous devez vous connecter pour poster un commentaire.Les derniers messages

2021-10-21 18:20:19
Picture 1 from YeneTube 2021-10-21 18:20:19
ዛሬ በመቀሌ ተጨማሪ የአየር ድብደባ መካሄዱን መንግስት አስታወቀ!

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዛሬ ከቀትር በኋላ በመቀሌ ከተማ በሚገኘው የቀድሞው የሰሜን እዝ ዋና መቀመጫ ግቢ ላይ የአየር ድብደባ ማካሄዱን መንግስት ይፋ አደረገ።

የመንግስት ኮሚንኬሽን አገልግሎት ኃላፊ የሆኑት ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) የአየር ድብደባው ከቀትር በኋላ መካሄዱን ለሪፖርተር አረጋግጠዋል።

የአየር ድብደባው የተካሄደው ቀደም ሲል የአገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን እዝ ዋና መቀመጫ በነበረው እና በአሁኑ ወቅት የህወሓት ኃይል ለወታደራዊ አገልግሎት በሚጠቀምበት ግቢ ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
13.1K viewsedited  
Ouvert / Commentaire
2021-10-21 14:34:49 የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን 700 ሚሊየን ብር ፈሰስ ከሚያደርግ የመኪና አምራች ድርጅት ጋር የስምምነት ውል ተፈራረመ፡፡

ኮርፖሬሽኑ ኤልአውቶ ኢንጂነሪንግ እና ትሬዲንግ ከተሰኘ የመኪና አምራች ድርጅት ጋር በድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ መኪና በመገጣጠም ለሀገር ውስጥ እና ለውጪ ገበያ ለማቅረብ ዛሬ በኮርፖሬሽኑ ፅ/ቤት የውል ስምምነት ፈፅሟል፡፡የውል ስምምነቱን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ እና የኤልአውቶ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ በቀለ አበበ ተፈራርመዋል፡፡

ዛሬ በነበረው የፊርማ ስነ-ስርዓት ላይ የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ ካለፈው በጀት አመት ጀምሮ የሀገር ውስጥ ድርጅቶችን ወደ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለማስገባት ጠንከር ያሉ ስራዎች እንደተሰሩ የገለፁ ሲሆን የዛሬው የውል ስምምነትም የጥረቱ አካል ውጤት ነው ብለዋል፡፡ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለውም ድርጅቱ እስካሁን በፓርኮቻችን ላይ እየሰሩ ካሉ ድርጅቶች በይዘቱ ለየት ያለ መሆኑን ገልጸው በታቀደው ግዜ ወደ ስራ እንደሚገባ ተስፋ አደርጋለሁ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የኢልአውቶ ኢንጂነሪንግ እና ትሬዲንግ ኃ/የተ/ የግል ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ በቀለ አበበ በበኩላቸው ድርጅታቸው ባገኘው እድል ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው የመረጡት የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ የተሟላ አገልግሎቶች ስላሉት ለምርት ሂደታቸው ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ሲሆን ፓርኩ ከጅቡቲ ወደብ ያለው ርቀትም አጭር በመሆኑ ለስራ ቅልጥፍና ትልቅ ፋይዳ አለው ሲሉ ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ በቀለ አበበ ተናግረዋል፡፡

ድርጀቱ በ700 ሚሊዮን ብር የሚያቋቁመው የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር ለ400 ዜጎች ጊዜያዊ እና ቋሚ የስራ እድል በመፍጠር በዓመት 9000 መኪኖችን ለሀገር ውስጥ አና ለውጪ ገቢያ እንደሚያቀርብ ተገልጿል፡፡ኤልአውቶ ኢንጂነሪንግ እና ትሬዲንግ 11ሺ ካ.ሜ ስፋት ያለው ሼድ ለመውሰድ የኪራይ ውል ስምምነት ያደረገ ሲሆን 50 በመቶ ምርቶቹን ለውጪ ገበያ (ኬኒያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ታንዛኒያ፣ ጅቡቲ እና ሶማሌ ላንድ) የሚያቀርብ ሲሆን ከፊሉን 50 በመቶ ምርቶቹን ደግሞ ለሀገር ውስጥ ገበያ የሚያቀርብ ይሆናል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
15.5K views
Ouvert / Commentaire
2021-10-21 13:37:02
Picture 1 from YeneTube 2021-10-21 13:37:02
እስክንድር ነጋ በደረሰበት ድብደባ ምክንያት ችሎት አለመቅረቡ ተገለፀ!

በእነ እስክንድር ነጋ ላይ ምስክሮችን ማሰማት የጀመረው የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፀረ ሽብር እና ሕገ-መንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ከትላንት የቀጠለ ቀጠሮ ለዛሬ ሰጥቶ የነበረ ሲሆን በጠዋቱ ውሎ አንደኛው ተከሳሽ ስንታየሁ ቸኮል ባቀረበው ሪፖርት መሰረት እስክንድር ነጋ በትናንትናው እለት ምሽት እስር ቤት ውስጥ በደረሰበት ድብደባ ምክንያት ችሎቱ ላይ ሊገኝ መገኘት አለመቻሉ ተጠቅሷል።

ሪፖርቱ እንደተሰማ የእነ እስክንድርን ችሎት ለመከታተል የመጡት ታዳሚዎች ተቃውሞ በማሰማት ችሎቱን አቋርጠው መውጣታቸውን እና ችሎቱ መቋረጡንም የባልደራስ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ በቃሉ አጥናፉ(ዶ/ር) ለአዲስ ዘይቤ አረጋግጠዋል።

አያይዘውም እስክንድር ላይ የደረሰውን ድብደባ መንስዔ እና ተጠያቂ አካላቱን ጉዳይ ለማጣራት ጠበቃዎቹ ወደ እስር ቤት መሄዳቸውን የገለፁልን ሲሆን ችሎቱን አቋርጠው የወጡት ታዳሚዎች በፖሊስ ተይዘው ወደ አምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዳቸውንም ነግረውናል።

[@AddisZeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
15.0K views
Ouvert / Commentaire
2021-10-21 13:16:43
Picture 1 from YeneTube 2021-10-21 13:16:43
አርቲስት መሰረት መብራቴ ለልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማዕከል ያሰባሰበችውን 6 ሚሊዮን ብር አስረከበች!

አርቲስት መሰረት መብራቴ በአሜሪካን ሀገር በነበራት ቆይታ ያሰባሰበችውን 6 ሚሊዮን ብር ለልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማዕከል በዛሬው ዕለት አስረክባለች፡፡

ገንዘቡ የልብ ህመም ላለባቸው 60 ህጻናት ህክምና የሚውል እንደሆነም ተገልጿል።

አርቲስቷ ላለፉት 3 ዓመታት በማዕከሉ በአምባሳደርነት እያገለገለች የምትገኝ ሲሆን ሕክምናን ለማግኘት ወረፋ እየጠበቁ የሚገኙ ህጻናትን ለመታደግ የተለያዩ የገቢ ማሰባሰብ ስራዎችን እየሰራች ትገኛለች።

በ1981 ዓ.ም የተመሰረተው የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማዕከል ላለፉት 32 ዓመታት ከ9 ሺ 500 በላይ ህጻናት ህክምና እንዲያገኙ ማድረጉን መረጃዎች ያሳያሉ።

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
14.2K views
Ouvert / Commentaire
2021-10-21 11:53:45
Picture 1 from YeneTube 2021-10-21 11:53:45
💯JOBS UPDATES CHANNEL

Get Daily Job Updates For Ethiopia Country.

Willing to work in Ethiopia ?
👉Then click to Join our channel here!

All Jobs are Legit and fowarded direct from AjiraNawe Website to the Channel.

Remember: We do not ask for money for you to get a job, we are just your helping hand to keep you updated with open vacancies released everyday.

Join Now and Thank Us Later.
Channel Link 👉 https://t.me/jobs_ethiopia
14.1K views
Ouvert / Commentaire
2021-10-21 11:30:03
Picture 1 from YeneTube 2021-10-21 11:30:03
ግብፅ እና ሱዳን የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ማካሄድ ጀመሩ!

የግብፅ እና የሱዳን ወታደራዊ ኃይሎች ከትናንት በስትያ ማክሰኞ የግብፅ ድንበር ጠባቂዎችና የሱዳን እግረኞችን ያካተተ የጋራ ልምምዶች መጀመራቸውን የግብፅ ጦር አስታወቋል።የጋራ ወታደራዊ ልምምዱ በሜድትራኒያን ግዛት በማትሮህ ግዛት በመሐመድ ናጉይብ የጦር ሰፈር መካሄዱም ተገልጿል።

ወታደራዊ ልምምዱ እስከ ጥቅምት 29 ድረስ እንደሚቀጥል የግብፅ ወታደራዊ ቃል አቀባይ ገብር አብደል ሃፌዝ መናገራችውን ሲጂቲን በድረገጹ አስነበቧል።

የመጀመሪያ ደረጃ ንድፈ ሃሳባዊ ንግግሮችን ጨምሮ ተግባራዊ ልምምዶችን እንዲሁም የድንበር ደህንነትን ለመጠበቅ እና ሰርጎ ገብነትን ለመዋጋት የሚያገለግሉ የጦር መሳሪያዎች የሚያጠቃልል ነው።አሁን የሚካሂደው የጋራ ልምምድ የሁለቱን ሃገራት የጋራ ዕድገት የማጠናከር ዓላማ ያለው ሲሆን ግብጽ ከወዳጅ አገራት ጋር ወታደራዊ ትብብርን ለማሳደግ ያላት ዕቅድ አካል ነውም ተብሏል።

✍Asham
@YeneTube @FikerAssefa
13.5K views
Ouvert / Commentaire
2021-10-21 10:52:43
Picture 1 from YeneTube 2021-10-21 10:52:43
ከቡና ወጪ ንግድ ከእቅድ በላይ ተጨማሪ 120 ሚሊየን ዶላር ተገኘ!

በበጀት አመቱ የመጀመሪያ ሩብ ከቡና ወጪ ንግድ 330 ሚሊየን ዶላር በገኘቱን የቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) ለካፒታል ጋዜጣ ተናገሩ፡፡የገቢ መጠኑ በተጠቀሰው ጊዜ ይገኛል ተብሎ ከተጠበቀው መጠን ከግማሽ በላይ ጭማሪ የታየበት ነው፡፡

በሩብ አመቱ ልናሳካ ካቀድነው ተጨማሪ 120 ሚሊየን ዶላር አግኝተናል በዚህ ከቀጠልን በበጀት አመቱ በቀላሉ የአንድ ቢሊየን ዶላር ገቢን እናሳካለን፤ ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ አክለዋል፡፡

የብራዚል የቡና ምርት በአየር ንብረት ምክንያት መጎዳት የአለም የቡና ዋጋ እንዲያሻቅብ እያደረገው መሆኑ ይጠቀሳል፡፡ይህም ለገቢ ማደግ አስተዋፅኦ እንደነበረው የተገለጸ ሲሆን ፤በተጨማሪም ኢትዮጵያ የምትልከውን ቡና በከፍተኛ መጠን እየጨመረች ከመሆኑ ጋር ተያዞ የገቢ መጠኑን እያሳደገው ነው፡፡

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
13.4K views
Ouvert / Commentaire
2021-10-21 09:35:04
Picture 1 from YeneTube 2021-10-21 09:35:04
በትግራይ ክልል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ያላቸው ደንበኞች ላይ የተጣለው እገዳ መነሳቱ ተነገረ!

በትግራይ ክልል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የባንክ ሂሳብ ከፍተው ከጦርነቱ በኋላ ሂሳባቸው የታገደባቸው ደንበኞች አሁን እገዳው እንደተንሳላቸውና ሂሳባቸውን ማንቀሳቀስ እንዲችሉ መፈቀዱን ዋዜማ ራዲዮ ሰምቻለሁ ብላለች።

አንድ ዓመት ሊሆነው የተቃረበው ጦርነት መጀመሩን ተከትሎ በትግራይ ክልል ያለው የባንክ አገልግሎት ሲቋረጥ በትግራይ ክልል የተከፈቱ የባንክ ሂሳቦች እንደይንቀሳቀሱ አብረው መታገዳቸው ይታወሳል።ለእገዳው ምክንያት የነበረው ከፀጥታ ስጋት ጋር የተያያዘ የገንዘብ ዝውውርን መግታት ነበር።

አንድ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፍተኛ የስራ ሀላፊ ለዋዜማ እንደተናገሩት ትግራይ ክልል ሂሳብ የከፈቱ ደንበኞቹ የታገደባቸውን ሂሳብ ለማንቀሳቀስ ከፈለጉ አቅራቢያቸው ባለ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ቀርበው የታገደባቸውን ሂሳብ ማንቀሳቀስ እንዲፈቀድላቸው የሚጠይቅ ማመልከቻ በመጻፍና ከማመልከቻው ጋርም ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያን እንዲሁም የሂሳብ ደብተራቸውን በማያያዝ ጥያቄያቸውን ማቅረብ ይችላሉ።ባንኩም አስፈላጊውን ማጣሪያ አድርጎ ደንበኞቹ ሂሳባቸውን እንዲያንቀሳቅሱ ያደርጋል።

ትግራይ ክልል ተከፍተው በጦርነቱ ሳቢያ መንቀሳቀስ ያልቻሉ ሂሳቦችን እንዲንቀሳቀሱ የማድረጉን ስራ ግን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውጭ ሁሉም የግል ንግድ ባንኮች ስለመጀመራቸው ዋዜማ ራዲዮ ማረጋገጥ አልቻለችም። ያነጋገርናቸው የአንድ የግል ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት ስለ ጉዳዩ መረጃ እንደሌላቸው ተናግረዋል።

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
14.5K views
Ouvert / Commentaire
2021-10-21 09:20:02
Picture 1 from YeneTube 2021-10-21 09:20:02
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ 'ትሩዝ ሶሻል' የተባለ አዲስ ማኅበራዊ ሚዲያ ሊመሠርቱ መሆኑን አስታወቁ።

ትራምፕ ማኅበራዊ ሚዲያው በአሜሪካ የተቃዋሚ ድምጾችን ዝም በማሰኘት የሚታወቁ "ታላላቅ የቴክኖሎጂ ጭቆና ያስቆማል" ብለዋል።ትራምፕ የሚመሩት ትራምፕ ሚዲያ እና ቴክኖሎጂ ቡድን (ቲኤምቲጂ) በደንበኝነት ምዝገባ ቪዲዮ-በፍላጎት የሚሰጥ አገልግሎት ለማስጀመር አስቧል።በጥር ወር ደጋፊዎቻቸው የአሜሪካን ምክር ቤት ህንጻን ካፒቶል ሂልን በመውረራቸው ምክንያት ትራምፕ እንደ ትዊተር እና ፌስቡክ ካሉ ታዋቂ የማኅበራዊ ሚዲያ ትስስር መድረኮች በጊዜያዊነት ወይም በቋሚነት ታግደዋል።

እሳቸው እና አማካሪዎቻቸው ከዚያ በኋላ ተፎካካሪ የማኅበራዊ ሚዲያ ለመፍጠር ስለማቀዳቸው ፍንጭ ሰጥተዋል።በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ 'ከዶናልድ ጄ ትራምፕ ዴስክ' የሚባል ድረ-ገጽ ጀምረው ነበር።ድረ-ገጹ ከተጀመረ ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ እስከወዲያኛው ተዘግቷል።

በቲኤምቲጂ መግለጫ መሠረት 'ትሩዝ ሶሻል' በሚቀጥለው ወር ለተመረጡ ሰዎች ብቻ ክፍት ሆኖ በአውሮፓውያኑ 2022 የመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት ደግሞ በአገር አቀፍ ደረጃ ይለቀቃል ተብሏል።ትራምፕ "ታሊባን በትዊተር ላይ ትልቅ ቦታ ኖሮት ተወዳጁ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዝም እንዲል በተደረገበት ዓለም ውስጥ እየኖርን ነው" ሲሉ ጽፈዋል።"ሁሉም ሰው ለምን ትልልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን አትገዳደሩም ብሎ ይጠይቀኛል? ደህና፣ በቅርቡ ይሆናለን!" በማለት አክለዋል።
አዲሱ ኩባንያ የሚሠራ ገጽ እንዳለው የሚጠቁም ነገር የለም።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
13.4K views
Ouvert / Commentaire